ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሶሪያዊያን ልጆች በስደት ላይ ተወልደዋል ተባለ፡፡

ላለፉት 10 ዓመታት በእርስ በርስ ጦርነት የምትታመሰዉ ሶሪያ በርካታ ዜጎቿ ለስደት ተዳርገዋል፡፡

ወደ 20 ሚሊየን የሚሆን ህዝብ እንዳላት የሚነገርላት ሶርያ አብዛኛው ህዝቧ አሁንም ድረስ በስደተኛ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

የሶርያ የእርስ በርስ ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከአንድ ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ልጆች በስደት ላይ እንደተወለዱም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሶርያ ወደ ጦርነት ከገባች አስር አመት የሆናት ሲሆን በጦርነቱ ምክንያት ከግማሽ በላይ የሚሆነው ህዝቧ ለስደት ተዳርጓል ነዉ የተባለዉ፡፡

አሁን ላይ ወደ 5 ነጥብ 7 የሚጠጋ የሀገሬው ህዝብ በሀገር ወስጥ ስደት እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

አብዛኛው ስደተኛም ወደ ጎረቤት ሀገራት የተጠለሉ ሲሆኑ በቱርክ፣ ጆርዳን እና በሊባኖስ በርካታ ሶርያዊያን ስደተኞች እንዳሉ ነው የተነገረው፡፡

የሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት መቋጫ ሊያገኝ ያልቻለዉ በሁለቱም ወገን በዉጭ ጣልቃ ገብነት ስለሚደገፉ መሆኑ ይነገራል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *