ኳታር በአፍጋኒስታን የሰላም ውይይት ላይ እንደምትሳተፍ አስታወቀች፡፡

የአፍጋኒስታን የሰላም ዉይይት የምታዘጋጀዉ ሩሲያ ስትሆን በዉይይት መድረኩ ላይ እንደምትሳትፍ አስታውቃለች፡፡

ይህን ያረጋገጡት የኳታር ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ሙታሊክ አልቃታኒ ናቸዉ፡፡

አፍጋኒስታን ሰላም እንድትሆን ኳታር የበኩሏን ትወጣለች ያሉት አምባሳደሩ ሞስኮ በሚዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ ሀገራቸው በርግጠኝነት ትሳተፋለች ብለዋል፡፡

ጦርነት ያቆሰላት አፍጋኒስታን ሰላም ከራቃት ሁለት አስርት አመታት ልታስቆጥር ነው፡፡

ከሰሞኑ ሩስያ የአፍጋኒስታን ጦርነት እንዲያበቃ ከበርካታ ሀገራት ጋር በመሆን የተለያዩ ውይይቶችን እያደረገች እንደምትገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ከታሊባን ጋር እስጣ ገባ የገባው የአሜሪካ ወታደርም ሀገሩን ለቆ እንዲወጣ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ማሳወቃቸው የሚታወስ ነዉ፡፡

ሞስኮ የምታዘጋጀው የአፍጋኒስታን የሰላም የምክክር መድረክ የፊታችን ሀሙስ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
አልጀዚራ

በሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *