በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ ፅንፈኛ ሓይሎች ምክንያት የሚደርሰዉን ሰብአዊ ቀዉስ የፈደራልና የክልል መንግስታት በመተባበር እንዲያስቆሙ አብንና ባልደራስ ጠየቁ፡፡

አብንና ባልደራስ በቀጣዩ ምርጫ በትብብር ለመስራት መፈራረማቸዉን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በዚህ መግለጫቸዉም በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ ፅንፈኛ ሓሎች ምክንያት ዜጎች ለሞት፤ አካል ጉዳት፣ መፈናቀል እየተዳረጉ ነዉ፤ከፍተኛ ንብረትም እየወደመ ነዉ፤ይህን ለማስቆምም የፌደራል እና የክልል መንግስታት ተግተዉ እንዲሰሩም ጠይቀዋል፡፡

በሁለቱ ፓርቲ አመራሮች መካከል ለወራት ሲካሄድ የነበረዉ ድርድር ተጠናቆ ምርጫዉን በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ የሚያስችል ስልት መቀየሳቸዉንም በዛሬዉ እለት በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል፡፡

ከዚህ በፊት በጋራ አብሮ ለመስራት ያልቻሉ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች፤ አሁንም ጊዜዉ ባለመርፈዱ ፍላጎት ካላቸዉ ለመቀበል ዝግጁ ነን ብለዋል ፓርቲዎቹ፡፡

ፓተርቲዎቹ አሁን የፈጠሩት ህብረት ለሌሎች አርአያ መሆን የሚችና ከትናንት የተሻለ የፖለቲካ ባህል ማሳያ ፈር ቀዳጅ እንደሚሆንም አመልክተዋል፡፡

ከምርጫዉ በኋላም ትብብሩ ጎልቶ የአገሪቱን ህዝብ ለዘመናት የቆየ የፍትህ ትግል ዳር ለማድረስ እንቀሳቀሳለን ነዉ ያሉት፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አለም አቀፍ አመራርነት ለመስጠት ከወዲሁ አብረን ቆመናል ብለዋል፡፡

አብን እና ባልደራስ የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ እራስን በራስ የማስተዳደር ዲሞክራሲያዊ መብት አክብረዉ ከሚቀበሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ትብብር በመፍጠር ዜጎች በፌደራል መንግስት ዉስጥ ዉክልና እንዲኖራቸዉ ጥምረቱ ሚና ይኖረዋልም ተብሏል፡፡

ፓርቲዎቹ ያላግባብ ተወንጅለዉ ለእስር የተዳረጉትንና የመምረጥና የመመረጥ መብታቸወን የተፈጉት የባልደራስ አመራሮችም በአስቸኳይ ይፈጡልን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የትግራይ ክልልን በተመለከተ ባነሱት ሃሳብ፣ ትህነግ በለኮሰዉ ጦርነት በትግራይ ክልል ባለዉ የህግ ማስከበር ዘመቻ፣ የንፁሃን ዜጎች ደህንነት እንዲጠበበቅና የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዳይደርስ ልዩ ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *