ባለፉት 8 ወራት ከ190 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚንስቴሩ እንዳለዉ በ2013 በጀት ዓመት ስምንት ወራት ውስጥ 191 ነጥብ 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከእቅድ በላይ 191 ነጥብ 45 ቢሊዮን ተሰብስቧል ብሏል፡፡

ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ24 ነጥብ 63 ቢሊዮን ብር ወይንም የ14 ነጥብ 76 በመቶ ዕድገት ማሳየቱንም ጠቁሟል፡፡

ገቢዉ የተሰበሰበዉም ከሀገር ውስጥ ታክስ 116 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ፣ ከውጭ ቀረጥና ታክስ 74 ነጥብ 59 ቢሊዮን ብር እና ከሎተሪ ሽያጭ የተጣራ 154 ነጥብ 46 ሚሊዮን ብር መሆኑን አስታዉቋል፡፡

ሚንስቴሩ እንዳለዉ የኮሮና ወረርሽኝና ለ3 ወራት ያህል የሕግ ማስከብር ዘመቻ በትግራይ ክልል በመደረጉ ምክንያት ገቢ ሰብሳቢ ተቋሞች ገቢ መሰብሰብ አለመቻላቸዉን እንደ ችግር አንስቷል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 09 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *