ቻይና አሜሪካን አስጠነቀቀች፡፡

ከሰሞኑ አሜሪካ የጦር መርከቦቿን ወደ ታይዋን የባህር ሰርጥ አስጠግታለች፡፡
ይህ አካባቢ ታይዋንን ከቻይና የሚለይ አካባቢ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የአሜሪካ የጦር መርከቦች በዚህ አካባቢ የሚሰማሩ ከሆነ ቻይና ወደ ታይዋን እንደፈለጋት የምታደርገዉን ጉዞ የሚገድብ መሆኑ ነዉ የተነገረዉ፡፡

ድርጊቱ ታይዋን ራሷን የቻለች ሀገር እንደሆነች እንዲሰማት የሚያደርግና እንደዛም እንድታስብ የሚገፋፋ በመሆኑ በፍጹም ተቀባይነት የለዉም ስትል ቻይና አሜሪካን ወቅሳለች፡፡

ከዚህ ድርጊቷ እንድትቆጠብና በአካባቢዉ የተጠጉ የጦር መርከቦቿን እንድትመልስም አስጠንቅቃለች፡፡
አሜሪካ በበኩሏ አካባቢዉን የመቆጣጠር ሃላፊነቱ የቻይና ሳይሆን የታይዋን ነዉ ስትል ገልጻለች፡፡

ሁለቱ ሀገራት በታይዋን ጉዳይ በተደጋጋሚ እየተወዛገቡ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ፕሬስ ቲቪ

በሙሉቀን አሰፋ
መጋቢት 09 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *