መጋቢት 19 በአዲስ አበባ ህዝባዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው፡፡

‹‹ መርከባችን አትሰምጥም ›› በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ሰልፍ ሊደፈረግ መሆኑ ተገለፀ

በኢትዮጲያ የውስጥ ጉዳይ ላይ በመግባት የዕጅ መጠምዘዝ ስራ ለመስራት በሚሞክሩ ተቋማት እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ እንዲስተጓጎል በሚሰሩ አካላት ላይ ተቃውሞ ለማሰማት ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የሰላማዊ ሰልፉ ዋነኛ አላማ የኢትዮጲያ ህዝብ በሀብቱ ለመጠቀም የማንንም ፈቃድ የማይሻ እና በዚህ ጉዳይ ላይ የማይደራደር መሆኑን ለዓለም ህዝብ ለማሳወቅ ነው ተብሏል፡፡

ስለ ኢትዮጲያ ትክክለኛ መረጃ ለዓለም እንዳይደርስ በሚሰሩ ሀገራት እና አለምአቀፍ ሚዲያዎች ላይ ተቃውሞ ለማሰማት ህዝባዊ ሰልፍ ለማዘጋጀት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን አስተባባሪ ኮሚቴዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ አሳዉቀዋል፡፡

በመሆኑም መላ የሃገሪቱ ህዝብ እና የኢትዮጲያ ወዳጅ የሖኑ የውጭ ሀገር ዜጎች እና ተቋማት ህዝባዊ ሰልፍ በሚከናወንበት እለት አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ሰላማዊ ሰልፍ የፊታችን መጋቢት 19 የሚደረገ ሲሆን በመስቀል አደባባይ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል ተብሏል፡፡

የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴዎች እንደተናገሩት፣ ህዝባዊ ሰልፉን ለማድረግ የሚመለከታቸው አካላት ፈቃድ እንዲሰጣቸው ከሳምንት በፊት ያቀረቡ ሲሆን፣ ተቋሙ ተቀብሏቸው የራሱን ዝግጅት እያደረገ ይገኛል ሲሉ ኮሚቴዎቹ ገልፀዋል፡፡

በሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.