ፑቲን ጆ ባይደንን በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ላይ እንጋጠም ብለዋቸዋል፡፡

ይህ ሳምንት ለአሜሪካ እና ሩሲያ ግንኙነት በጣም አስቸጋሪ ሆኗል፡፡
የሞስኮው ቭላድሚር ፑቲን እርሳቸውና ጆን ባይደን ዛሬ ወይም ሰኞ ቀጥታ ውይይት እንዲያደርጉ ጠይቀዋቸዋል፡፡
“ፕሬዝዳንት ባደንን ውይይቶቻችን እንዲቀጥሉ ለመጋበዝ እፈልጋለሁ ፣ ግን ይህ ወይይት ምንም መዘግይት ሳይኖረው ግልጽና ቀጥተኛ በሆነ መንገድ እንዲሆን እፈልጋለሁ” ብለዋል ፕሬዝደንቱ ከሩሲያ 24 የቴሊቪዥን ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቆይታ፡፡

ፑቲን እንደሚሉት “ጉዳዩን ቸል ልለው አልችልም ፤በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ታይጋ ደን ሄጂ እረፍት ማድረግ እፈልጋለሁ ፤ስለዚህ ክርክሮ ዛሬ ወይም ሰኞ ይሆናል ”ብለዋል፡፡
ፕሬዝደንት ፑቲን አክለውም “የአሜሪካው ፕሬዝደንት በሚመቸው በማንኛውም ጊዜ ውይይቱን ለማድረግ ዝግጁ ነኝ” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
ጆ ባይደን የሩሲያውን ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲንን ገዳይ ነው ሲሉ ማብጠልጠላቸውን ተከትሎ በሞስኮ እና ዋሽንግተን መካከል ያለው ትኩሳት ዳግም ተቀስቅሷል፡፡

ባይደን ፑቲን በ2020 የአሜሪካ ምርጫ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት መሞከራቸው ዋጋ ያስከፍላቸዋል ብለዋል ከኤቢሲ ኒውስ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ፡፡
ሩሲያ ይህንን ተከትሎ በአሜሪካ ያሉትን አባሳደሯን ለምክክር በሚል ጠርታለች፡፡
ቭላድሚር ፑቲን ጆ ባይደን ፍቃዳቸው ከሆነ በቴሌቪዥ በቀጥታ ስርጭት ይግጠሙኝ ብለዋል፡፡
የአሜሪካ የደህንነት መሥሪያ ቤት ያወጣውን ሪፖርት ተከትሎ በቀጣዩ ሳምንት በሩሲያ ላይ ማዕቀብ ልትጥል ትችላለች እየተባለ ነዉ፡፡

(አናዱሉ)

በያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.