አሜሪካ ሶማሊያን አስጠንቅቃለች፡፡

አሜሪካ ሶማሊያን ያስጠነቀቀችው ምርጫ እንድታደርግ ነው፡፡

ሶማሊያ ባፋጣኝ ምርጫ እንድታደርግ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስጠንቅቋል፡፡

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ቢሊከን ሶማሊያ ያራዘመችውን ምርጫ በፍጥነት እንድታደርግ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለው ሀገሪቷ ግልጽ እና አካታች የሆነ ምርጫ በቅርቡ ማድረግ አለባት ነው ያሉት።

ሀገሪቷን በመምራት ላይ የሚገኙት አብዱላሂ ሞሀመድ ፋርማጆም ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በጋራ በመሆን በሀገሪቱ የተፈጠረውን አለመረጋጋት እንዲያረግቡም ጠይቀዋል፡፡

ሶማሊያ ልታደርገው የነበረው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በሀገሪቱ ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ማራዘሟ ይታወሳል፡፡

ምርጫው መራዘሙን ተከትሎም በሀገሪቱ ግጭት እንደ አዲስ መቀስቀሱም የሚታወስ ነው፡፡

ይህን ግጭት በዘላቂነት እልባት ለመስጠት ደግሞ ምርጫዉ መካሄድ እንዳለበት አሜሪካ ገልጻለች ።

ሲ ኤን ኤን

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 11 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.