ለዝግጅቱ የኬንያ ፣ የደቡብ አፍሪካ ፣ የዚምባብዌ ፣ የኮሞሮስ ፣ የሞዛምቢክ ፣ የዛምቢያ እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንቶችን ጨምሮ በርካታ የአፍሪቃ ሀገራት መሪዎች ተገኝተዋል ፡፡
ፕሬዝደንት ማጉፉሊ ባለፈው ረቡዕ ከልብ ህመም ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ማለፉን ባለስልጣናት መናገራቸው የሚታወስ ነው ይላል የቢቢሲ አፍሪቃ ዘገባ፡፡
ሀገሪቱ ለሟቹ ፕሬዝደንት ማጉፉሊ ያዘጋጀችው የመሰናበቻ ዝግጅት ሶስተኛ ቀኑን ይዟል፡፡
በዶዶማ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ አስክሬናቸውን ለመሰናበት በመጠባበቅ ላይ ቢሆኑም ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን ይህን ለማድረግ እንደማይቻል አሳውቀዋል፡፡
ከዚህ ይልቅ አስከሬኑ በስታዲየሙ ዙሪያ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ህዝቡ እንዲያይና እንዲሰናበታቸው ይደረጋል ነው ያሉት፡፡
በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በንግድ መዲናዋ ዳሬሰላም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች አስከሬኑ ሲዘዋወር ለመሰናበት መንገዶችን አጥለቅልቀዉ እንደነበር ተነግሯል፡፡
አሁንም ብዙዎች አስከሬኑ ለሕዝብ እይታ ወደ ተቀመጠበት ዋና እስታዲዬም ተገኝተዋል ሲል ቢቢሲ አፍሪቃ ዘግቧል፡፡
በያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ.ም











