በሰባት ቀናት ብቻ ከ53 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ለኢቲዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ፣ የኮንትሮባንድ እቃዎች የተያዙት ከቀን 3 /2013 ዓ.ም እስከ 9/ 2013 ዓ.ም ድረስ ነዉ፡፡
በዚህም ግምታዊ ዋጋቸው ከ53 ሚሊዮን 27 ሺህ ብር በላይ የኮንትሮባድ እቃዎች መያዛቸዉን ሰምተናል፡፡
የኮንትሮባድ እቃዎቹ በህገወጥ መንገድ ከሃገር ሊወጡ እና ወደሃገር ዉስጥ ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆኑ አብዛኞቹ ወደሀገር ሊገቡ ሲሉ መያዛቸዉን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከኮንትሮባንድ እቃዎቹ መካከልም የተለያዩ አልባሳት፣ ምግብ ነክ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሲጋራ፣ ኮስሞቲክስ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ ጫማ፣ መድሃኒት፣ መለዋወጫና ልዩ ልዩ አደንዛዥ ዕፆች እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ ሀዋሳ፣ ጅጅጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሞያሌ ፣ኮምቦልቻ እና አሶሳ የኮንትሮባንድ እቃዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉባቸው የጉምሩክ ቅርንጫፎች መካከል ተጠቃሾች ናቸዉ፡፡

በረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.