የጎርፍ አደጋዉ የተከሰተዉ በምስራቃዊ የሃገሪቱ የባህር ዳርቻ ሲሆን፣ በአካባቢዉ በተከታታይ የጣለዉን ከፍተኛ ዝናብን ተከትሎ አደጋዉ መከሰቱ ተነግሯል፡፡
የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት ሞሪሰን፣በአደጋዉ ለተጎዱ ሰዎች አፋጣኝ ድጋፍ እንዲደረግ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡
አሁን ላይ የተከሰተዉ የጎርፍ አደጋ ከ 50 ዓመታት ወዲህ በሃገሪቱ ተከስቶ የማያዉቅ ከባድ አደጋ መሆኑን የሃገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
የአካባቢዉ አስተዳዳሪ ግላዲየስ በርጂለያን፣ በሰደድ እሳት እና በድርቅ አደጋ ሲማቅቅ በቆዬ ማህበረሰብ ላይ ይህ አደጋ መከሰቱ እጅግ አሳዛኝ ነዉ፤ ይህንም በጋራ ሆነን እንዳለፉት አስቸጋሪ አደጋዎች ሁሉ እንሻገረዋለን ብለዋል፡፡
የአወስትራሊያ ሜትኦሮሎጂ ቢሮ እንዳለዉ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ብቻ ይስተዋል የነበረዉ 1 ሺህ ሚሊ ሜትር ከባድ የዝናብ መጠን በአሁኑ ወቅት በበርካታ አካባቢዎች ላይ እየተከሰተ ይገኛል ብሏል፡፡
ፍራንስ 24
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሙሉቀን አሰፋ
መጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ.ም











