የሪፐብሊክ ኮንጎ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ የነበሩት ጉዬ ፓርፌት ኮሌላስ በኮሮና ቫይረስ መሞታቸው ታዉቋል፡፡
ኮሌላስ በትላንትናው እለት ለተጨማሪ ህክምና ወደ ፈረንሳይ በማቅናት ላይ እያሉ ነው በህክምና አውሮፕላን ውስጥ ህይወታቸው ያለፈው፡፡
በሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለመሳተፍ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ብርቱ ፉክክር ሲያደርጉ የነበሩት ጉዬ ኮሌላስ፣ በምርጫው ዋዜማ ላይ ነበር ሆስፒታል የገቡት፡፡
የኮሌላስ ቤተሰቦች ዓርብ እለት ብራዛቢል ወደ ሚገኝው የግል ሆስፒታል እንደተወሰዱና ኮሮና ቫይረስ እንደያዛቸውም ተናግረዋል፡፡
አሶሼትድ ፕረስ
በሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ.ም











