ለትግራይ ክልል መልሶ ግንባታ 40 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል ተባለ፡፡

በትግራይ ክልል በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ በኋላ ክልሉን መልሶ ለመገንባት 40 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገልፀዋል።

በህግ ማስከበር ሂደት ምክንያት በርካታ መሠረተ ልማቶች እንደወደሙ ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ እነዚህን መሠረተ ልማቶች ለመጠገን መንግስት ከፍተኛ ወጪ እያወጣ ይገኛል ነው ያሉት።

ከመሠረተ ልማቶች ጥገና በተጨማሪም 70 በመቶ የሚሆነውን የሰብአዊ እርዳታ የተደረገው በኢትዮጵያ መንግስት ነው ብለዋል ።

በዚህም ኢትዮጵያ አንድ ቢሊዮን ዶላር ወይንም 40 ቢሊዮን ብር ወጪ እንድታወጣ ሆኗል ብለዋል።

የውጭ እርዳታ ሰጪዎች ክልሉ ለተራድኦ ድርጅቶ ክፍት ይሁን ያሉ ቢሆኑም ከተከፈተ በኋላ ግን ገብተዉ እርዳታ እየሰጡ አለመሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *