ሳዑዲ አረቢያ የየመን ጦርነትን ለማቆም የሚያስችል የሰላም ዕቅድ አቅርባለች፡፡

ለስድስት አመታት የዘለቀውን የየመን ጦርነት ለማስቆም ሳውዲ አረቢያ አዲስ የሰላም እቅድ ማቅረቧን አሳውቃለች፡፡

በሳውዲ መራሹ ጥምር ጦር በሚደገፈው መንግስት እና በኢራን በሚደገፉት የሀውቲ አማፅያን መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ሀሳብ አቅርባለች።

ይህ ዕቅድም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቁጥጥር የሚደረግበት እንደሆነም ነው የገለጸችው፡፡

ሳውዲ ባቀረበችው ዕቅድ መሠረትም ወሳኝ የተባሉ የአየር እና የባህር መግቢያዎችን በድጋሚ መክፈት እና የፖለቲካ ድርድር መጀመርን ይጨምራል ብሏል ቢቢሲ በዘገባው፡፡

የሀውቲ አማጽያን በበኩላቸው እቅዱ የተጣለውን የአየር እና የባህር እገዳ ለማንሳት የሚያስችል እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡

ዕቅዱ በሳዑዲ ዋና ከተማ ሪያድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ልዑል ፈይሰል ቢን ፈርሃን ይፋ መደረጎ ተነግሯል፡፡

የተፋላሚ ሀይሉቹ ግጭት የጀመረው በ2014 መገባደጃ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

ሪያድ በተባበሩት መንግስታት ዕውቅና ያለውን መንግሥት በመደገፍ በ 2015 ወታደራዊውን ጥምር ጦር በመምራት ነበር ጦርነቱን የተቀላቀለችው፡፡

ይሆን እንጂ አሁንም ድረስ ጠብ ያለ ውጤት ማስመዝገብ አልቻለችም፡፡

ሁለት ሦስተኛ ከሚሆነው የየመን ህዝብ ፣ 20 ሚሊዮን ዜጎች የሰብአዊ ዕርዳታ የሚሹ ናቸው ተብሏል፡፡

ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ህፃናት ደግሞ ከፍተኛ የምግብ እጥረት እንዳለባቸው ተነግሯል፡፡

በዚህ ግጭት ሳቢያም የየመን የጤና ሥርዓት ሙሉ ለሙሉ በመንኮታኮቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መቋቋም እንዳትችል እንዳደረጋት ተነግሯል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *