ስለክትባት መወራት ከተጀመረ በኋላ ህብረተሰቡ ውስጥ መዘናጋት በመምጣቱ ምክንያት የተጠቂዎች ቁጥር መጨመር እያሳየ ነው ተብሏል፡፡

በዛሬው እለት የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ክትባትን አስመልክቶ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

ወደ ሃገር ዉስጥ የገባው የአስትራዜኒካ ክትባትን በተመለከተ የገባው 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶዝ ካለው የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር አንፃር 20 በመቶው ብቻ ነው የሚያገኘው ተብሏል።

በተያዘው ፕሮግራም ከሱም ውስጥ ቅድሚያ 3 በመቶው ለጤና ባለሙያ እና በዙሪያው አገልግሎቱን ለሚሰጡና ከ18 እስከ 64 ያሉ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች በመጀመሪያው ረድፍ ይካተታሉ ተብሏል።

በሁለተኛው ረድፍ ደግሞ 17 በመቶው ተጋላጭ ተቋማትን ያካትታል ተብሏል።

ለምሳሌ በትራንፖርት ዘርፍ ላይ ያሉ፣ በኢንዱስትሪ ፖርኮች ላይ የሚሰሩ፣ ድንበር ተሻጋሪ የከባድ መኪና ሹፌሮች እና ከ 55 እስከ 64 አመት ላሉት መታቀዱ ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ 61 በመቶው የኮቪድ ተጠቂ ሴቶች ናቸው የተባለ ሲሆን ከተጠቂዎቹ 74 በመቶዎቹ ደግሞ ከ15 አስከ 44 አመት እድሜ ያሉት ናቸው ተብሏል።

በአሁኑ ወቅት ስለ ክትባቱ መወራት ከተመጀረ በኋላ መዘናጋት ተስተዉሏል ነዉ የተባለዉ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *