በማጉፉሊ የብሔራዊ የአስክሬን ሽኝት ወቅት 5 የቤተሰብ አባላት ተረጋግጠው መሞታቸው ተነግሯል፡፡

የቀድሞው የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ በትላንትናው እለት በዳሬሰላም አስከሬናቸው ለህዝብ እይታ በቀረበበት ወቅት ነው አንዲት ሴት እና አራት ልጆቿ በተፈጠረው ግርግር ተረጋግጠው የሞቱት ፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ ሀዘንተኞች በተጨናንቀው የኦሁሩ ስታዲየም ሲጋፉ ነው አደጋው የደረሰው ተብሏል፡፡

የታንዛኒያ የአካባቢው ዕለታዊ ጋዜጣ ሲቲዝን የተጎጂዎቹን የቤተሰብ አባል ሄንሪ ሙትዋን ጠቅሶ እንዲህ ብሏል: – “ወደ ሆስፒታል ሄደን ሁሉንም የሕመምተኞች ክፍል ፈልገን ነበር ነገር ግን ሱዛንና ልጆቿን ማግኘት አልቻልንም በኋላም ሀኪሞቹ ሄደን ጠየቅን እነሱን የአምስቱን አስከሬን ባገኘንበት የሬሳ ክፍል ውስጥ እንድንፈልጋቸው ነገሩን ያኔ እንደሞቱ አወቅን ብለዋል፡፡“

የ 30 ዓመቷ እናት ዕድሜያቸው 11 ፣ 8 ፣ 6 እና 5 ከሆኑ ልጆቿ ጋር ነው ህይወቷ ያለፈው፡፡

ትላንት ከመላው የአፍሪቃ አህጉር የተውጣጡ መሪዎች በታንዛኒያ ዶዶማ ከተማ ለሟቹ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የመጨረሻ አክብሮት ሽኝት ለማድረግ ተሰብስበው ነበር፡፡

ስታዲየሙ በውስጥም በውጭም የታጨናነቀ እንደነበር እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም የመጨረሻ የአክብሮት ሽኝት ለማድረግ ወረፋ ይዘው ታይተዋል፡፡

ጎረቤት ሀገር ለእኚህ የፖን አፍሪቃ አቀንቀኝ ብርቱ ሰው የስድስት ቀናት የሀዘን ቀን አውጃለች፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *