በኮሎራዶ አንድ ግለሰብ ፖሊስን ጨምሮ አስር ሰዎችን በገበያ ሥፍራ ተኩሶ መግደሉን ፖሊስ አስታወቋል።
ፖሊስ እንዳለው ጥቃት ፈጻሚው ግለሰብ በነበረው የተኩስ ልውውጥ ቆስሎ መያዙም ገልጻል።
ይህ ጥቃት ሲፈጸምም በዩቲዩብ ቀጥታ መተላለፉም ተነግሯል።
ጥቃቱ ያደረሰው ግለሰብ ወደ ገበያ አዳራሹ እንደገባ ነበር መተኮስ የጀመረው ይላል የቢቢሲ ዘገባ፡፡
ጥቃቱ የደረሰበት አካባቢ፣ ቦውልደር ፖሊስ ከ20 ደቂቃ በኋላ በትዊተር ገፁ ላይ “በኪንግ ሱፐርስ የገበያ ስፍራ ተኩስ የከፈተ ግለሰብ አለ” ሲል ጽፎ ነበር።
ከሁለት ሰዓት በኋላ ፖሊስ ሰዎች ከአካባቢው እንዲርቁ አስጠንቅቋል።
አክሎም “ምንም ዓይነት ቴክኒካዊ መረጃ ካያችሁ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አታሰራጩ” ሲል ትዊትር ሰሌዳው ላይ ነዋሪዎቹን ጠይቋል።
በያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም











