በኢትዮጵያ የቲቢ በሽታ እንዳለባቸዉ ከሚታሰቡ ሰዎች 29 በመቶ የሚሆኑት ወደ ጤና ተቋማት እየሄዱ አይደለም ተባለ፡፡

15ኛው አመታዊ የቲቢ ምርምር ጉባኤና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ39ኛ የሚከበረዉ የቲቢ ቀን መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በዚሁ መድረክ ላይ የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ እንደተናገሩት በዓመት 157 ሺህ ሰዎች በቲቢ እንደሚያዙ ይገመታል፡፡

ከዚህ ዉስጥ 29 በመቶ ያህሉ ወደ ህክምና እንዳልመጡ ነዉ ሚኒስትር ዲኤታዉ ዶክተር ደረጀ ድጉማ የተናገሩት፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቲቢ በሽታ እየተጠቁ ካሉ 30 ሀገራት አንዷ መሆኗን የተናገሩት ሚኒስትር ዲኤታ ዲኤታዉ ችግሩን ለመቀነስ አሁንም ከፍተኛ ጥረትን ይጠይቃል ብለዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.