በያዝነው ወር ብቻ ኢትዮጵያ 3 ቢሊዮን ብር የነዳጅ እዳ አለባት ተባለ፡፡

ኢትዮጵያ ለነዳጅ በዓመት እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር እንደምታወጣም ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አስታውቀዋል፡፡

ይህም የምታወጣው ወጪ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ እያደቀቀው ይገኛል ብለዋል፡፡

ሃገሪቱ በዓመት ከምታወጣው ወጪ ባሻገርም በያዝነው ወር ብቻም 3 ቢሊዮን ብር የነዳጅ ዋጋ እዳ እንዳለባት ተናግረዋል ፡፡

በዛሬው እለት 5ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድም በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በዛሬው እለት ካነሷቸው ሃሳቦች መካከል በሃገሪቱ በነዳጅ ዋጋ ላይ እየታየ የመጣውን ሁኔታ አንስተው የሽያጭ መሰረተ ልማት በቂ ያለመሆን፤ በሃገሪቱ የነዳጅ ዋጋ ላይ እየታየ ያለው የተደራሽነት ችግር እንዲሁም በነዳጅ አቅርቦቱ ላይ ያለው ከፍተኛ ጫና መኖሩን በማንሳት እነዚህ ችግሮች ከተሰራባቸው ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል አስታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በየዉልሰዉ ገዝሙ
መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *