ብሄራዊ ቡድኑ በወንበዴዎች ታገተ

የBelize እግር ኳስ ፌደሬሽን የብሄራዊ ቡድኑን አባላት የያዘው አውቶብስ በሄይቲ ወደ ሆቴሉ በመጓዝ ላይ ሳለ በታጣቂዎች መታገቱ ‹‹እንዳስከፋው›› ተናግሯል ክስተቱ የተፈጸመው ሰኞ እለት ነው፡፡

የቡድኑ አውቶብስ ወደ ሆቴሉ የሚያደርገውን ጉዞ እንዲቀጥል ለማስቻል አውቶብሱን አጅበው ሲጓዙ የነበሩ ፖሊሶች ከታጣቂ ቡድኑ ጋር ለመደራደር ተገደዋል፡፡

ካፕቴን ዲዮን ማክኮሊ አጋጣሚውን ‹‹ እጅግ አስፈሪ ›› ቅጽበት ብለውታል፡፡

‹‹ጉዳት የደረሰበት ሰው ባለመኖሩ ደስተኛ ነኝ፡፡ ስለ ጀግንነታችሁ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ›› በማለት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በፌደሬሽኑ ገጽ ላይ የተለጠፈው ምስል ወንበዴዎቹ በሞተር ሳይክሎች ላይ ተቀምጠው ፣ ፊታቸውን በጭንብል ሸፍነው እና መሳሪያ ታጥቀው ያሳያል፡፡

ቡድኑ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከሄይቲ ጋር በመጪው ሃሙስ በፖርት-አ-ፕሪንስ ለመጫወት ቀጠሮ ይዟል፡፡

ፊፋ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአቤል ጀቤሳ
መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *