ኢትዮጵያ በአሜሪካ የፀጥታ ድልድል ላይ እንደማትገባ ሁሉ አሜሪካም በኢትዮጵያ ጉዳይ ባትገባ ጥሩ ነው— ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ

የአማራ ልዩ ኃይል ከትግራይ ክልል ይውጣ የሚባለው ተቀባይነት እንደሌለውም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።

ኢትዮጵያ የትኛውንም የፀጥታ አካላትን በፈለገችው ቦታ የማስፈር እና የማንቀሳቀስ መብት እንዳላትም አንስተዋል።

የአሜሪካ መንግስት በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የፀጥታ ኃይሉን እንደሚያንቀሳቅስ ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስትም በፈለገው ክልል የማሰማራት መብቷ ሊጠበቅላት ይገባልም ብለዋል ።

የአማራ ክልል ልዩ ኃይል በትግራይ ክልል የተመደበው ፍልጎት ሳይሆን ክልሉን ለማረጋጋት እንደሆነ ያስገነዘቡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ አስፈላጊ ከሆነም ወደ ሌሎች ክልሎች ልናሰማራ እንችላል ነው ያሉት።

ነገር ግን የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ጥፋት ካጠፋ የማይጠየቅበት ምንም ምክንያት እንደሌለም አንስተዋል።

የሱዳንና የኢትዮጵያን ጉዳይ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ላይ
ጦርነት ለሱዳንም ለኢትዮጵያም አይበጅጅም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሱዳንም ሆነች ኢትዮጵያ ውጥታዊ ችግር ያሉባቸው አገራት ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ ወደ ጦርነት መግባት አይበጃቸውም ብለዋል።

ኢትዮጵያ እና ሱዳን ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸዉ አገራት በመሆናቸው ሊለያዩ እንደማይችሉም አንስተዋል።

ሱዳን ከየትኛውም አገር ጋር ወደጅነት መመስረት ብትችልም የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጋፋ ከሆነ ግን ስህተትና አደገኛ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *