ካናል ፕላስ በኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

ካናል ፕላስ በዘጠኝ ጣቢያዎች በኢትዮጵያ አገልግሎት ሊሰጥ ነው፡፡

ካናል ፕላስ የኢትዮጵያዊያን ታዳሚዎችን ፍላጎት ያማከሉ በአማርኛ ቋንቋ ፕሮግራሞቹን በቅርብ እንደሚጀምር አስታዉቋል፡፡

መቀመጫውን ፈረንሳይ ያደረገው ካናል ፕላስ በዓለማችን ካሉ ግንባር ቀደም ቴሌቪዥኖች አንዱ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በአፍሪካ ከ25 በላይ በሚሆኑ ሀገራት ውስጥ አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል፡፡

ካናል ፕላስ በአማርኛ ተዘጋጅተው ወደ ተመልካች የሚደርሱ የመዝናኛ፣ ትምህርታዊ እና መረጃ ሰጪ የሆኑ ፕሮግራሞች በቅርቡ ለመጀመር የተለያዩ ዝግጅቶች እያደረገ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው፡፡

ተቋሙ ከዚህም በተጨማሪ የሀገር ውስጥ ፊልሞች፣ ስፖርታዊ ክንዋኔዎች እና ዘጋቢ ፊልሞች በዘጠኝ ቻናሎች ሊያቀርብ እንደሆንም ነው ያስታወቀው፡፡

በአሁኑ ሰአት ተቋሙ በሰባት የሀገራችን ከተሞች ለስራ ብቁ የሆኑ የመስክ ሽያጭ እና የሳተላይት ዲሽ ቴክኒሽያኖችን በከፍተኛ ቁጥር በመመልመል እና በማሰልጠን ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅቱን እያጠናቀቀ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡

ዓለም አቀፍ የክፍያ ቴሌቪዥን አገልግሎት የሚሰጠውና በቅርቡ በኢትዮጵያ ስራውን የሚጀምረው ድርጅቱ 200 ለሚደርሱ ሰዎች የስራ እድል እንደሚፈጥር አስታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.