ምንያማር፡- ወደ አባቷ እቅፍ እየሮጠች ባለችበት ሰአት ከፖሊሰ በተተኮሰ ጥይጥ ሕይወቷ ያለፈው የ 7 አመት ህጻን

በምያንማር የ7 አመት ህጻን ወደ አባቷ እቅፍ እየሮጠች ባለችበት ሰአት ከፖሊሰ በተተኮሰ ጥይጥ ሕይወቷ ማለፉ ተገለጸ፡፡

ኪን ማዮ የተባለችው ይህቺው ህጻን ህይወቷ ሊያልፍ የቻለው በሀገሪቷ የነበረውን ህዝባዊ አድማ ለመበተን ፖሊስ የሃይል እርምጃዎችን በሚወስድበት ሰአት መሆኑ ተነግሯል፡፡

በምያንማር ቀውሱ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑ ነው የሚነገረው፡፡

ለተቃውሞ አደባባይ በሚወጡና ተቃውሞውን በሃይል ለማስቆም በሚሞክረው ፖሊስ መካከል በሚፈጠር ግጭት በርካታ ንጹሃን ዜጎች ለህልፈተ ህይወት እየተዳረጉ ነው፡፡

የሰባት አመቷ ህጻን ልጅ ደግሞ የቀውስ ከቁጥጥር ውጪ መሆን ማሳያ እንደሆመነ እየተነገረ ነው፡፡

በሀገሪቷ በተቀሰቀሰው አመጽ ከሞቱት ሰዎች መካከል የአሁኗ ህጻን በእድሜ ትንሷ ነች ተብሏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በጅብሪል ሙሓመድ
መጋቢት 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *