ኢራን የሳዑዲ መራሹ ጦር በየመን ላይ እያደረሰ ያለውን ጥቃት እንደምትቃወም ገለፀች፡፡

ድህነት ባጎሳቆላት የመን እየተከሰተ ላለው ግጭት ወታደራዊ እርምጃ መፍትሄ አይሆንም በማለት ኢራን አቋሟን አስታውቃለች፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ፣ በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው ወታደራዊ ሃይል በንፁሃኑ የየመን ህዝብ ላይ ጥቃት ማድረስ መቀጠሉን አጥብቆ አውግዟል፡፡

ባለፉት ስድስት ዓመታትም የወታደራዊ ጥቃቱ የመን ውስጥ 24 ሚሊዮን ሰዎችን ዒላማ አድርጓል ሲል መግለጫው ጠቅሷል፡፡

በሕክምና ማዕከላት በቦምብ ፍንዳታ ፣ በረሃብ ፣ በበሽታዎች ፣ በመድኃኒት እጥረት እና በነዳጅ እጥረት ሳቢያ በየቀኑ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሚሞቱም አስታውቋል፡፡

በጣም የከፋው ደግሞ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ የሚፈፀመው ድንገተኛ ጥቃት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት እንኳን ለአንድ አፍታ አለመቆሙ ነው ይላል መግለጫው፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በየመን ደም አፋሳሽ ለሆነው የሳዑዲ መሪዎችን ጥቃት ለማስቆም በሚደረገው ጥረት ላይ በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ላይም ጥርጣሬም እንዳለው አስታውቋል፡፡

እንዲሁም ከአንዳንድ ሀገራት የተውጣጡ ወታደራዊ ሃይላት ከሳውዲ ጋር በማበር በየመን ህዝብ ላይ በሚፈፀመው ወንጀል እና እልቂት ተባባሪ እየሆኑ ነው ሲል የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አመልክቷል፡፡
ፕረስ ቲቪ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በየዉልሰዉ ገዝሙ
መጋቢት 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *