ኮንቴነር የጫነች መርከብ ስዊዝ ካናልን ዘጋች፡፡

በግብጽ በሜድትራንያንና በቀይ ባህር መካከል መርከቦችን የሚያገናኘው ሰው ሰራሽ ቦይ ዝግ መደረጉን የካናሉ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

የስዊዝ ቦይ ከተሰራ ከ150 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን በአለም 10 በመቶ የሚሆነው የባህር ላይ የንግድ ልውውጥ የሚደረገው በዚሁ ካናል እንደሆነ ይነገራል፡፡

ባለስልጣኑ አሁን ለአገልግሎት ዝግ እንዲሆን የተደረገበት ምክንያት ካናሉ ማስተናገድ ከሚችለው በላይ 200 ሺህ ኮንቴነሮችን የተሸከመ መርከብ ለማለፍ ሙከራ በሚያደርግበት ሰአት መርከቡ ከቁጥጥር ዉጭ ሆኖ መስመሩን በመዝጋቱ ነዉ፡፡

መርከቡ 400 ሜትር ርዝመትና 59 ሜትር ስፋት እንዳለዉም ተነግሯል፡፡

ይህም ሌሎች መርከቦችን ለማሳለፍ አስቸጋሪ መሆኑን መረጃዉ ጠቁሟል፡፡

ይሄው ካናል በጣም መጨናነቅ የሚታይበት ሲሆን ለጊዜው ዝግ በመሆኑ የተነሳ ከ10 በላይ የሚሆኑ ኮንቴነር ተሸካሚ መርከቦች በአካባቢው ቆመው እንደሚገኙም ተነግሯል፡፡

ካናሉ እስከ መቼ ለአገልግሎት ክፍት ሊደረግ እንደሚችልም ባለስልጣናቱ የሰጡት ፍንጭ የለም፡፡
አልጃዚራ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.