ጆ ባይደን የሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል ማስወንጨፍ አሳሳቢ ነገር አይደለም ብለዋል፡፡

ባይደን አሜሪካ እና ሰሜን ኮሪያ ያላቸውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዲያጠናክሩ ፍላጎት እንዳላቸዉም አስታውቀዋል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሰሜን ኮሪያ የአጭር ርቀት ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏ አሜሪካን ለማስቆጣት እንደተደረገ አድርገው እንደማይቆጥሩት ነዉ የተናገሩት፡፡

ሰሜን ኮሪያ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ባሌይስቲክ ያልሆኑ ሚሳኤሎችን እንዳስወነጨፈች ተነግሯል፡፡

ድርጊቱ ሁሉ የተከናወነዉ ፒዮንግያንግ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በጋራ ወታደራዊ ልምምዶች ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው፡፡

የባይደን አስተዳደር ከሰሜን ኮሪያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመመሥረት መሞከራቸው እንደቀጠለ ቢሆንም በሰሜን ኮሪያ በኩል ግን ምንም አይነት ምላሽ እንዳላገኙ ይነገራል፡፡
ቢቢሲ

በየዉልሰዉ ገዝሙ
መጋቢት 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *