በሞዛምቢክ የዱቄት ዋጋ ቅሬታ አስነስቷል፡፡

በሞዛቢክ የዱቄት ዋጋ መናርን ተከትሎ የዳቦ ዋጋ ሊጨምር እንደሚችል የሀገሪቱ የዳቦ ጋሪሪዎች ማህበር አሳታውቋል፡፡

ማህበሩ እንዳለው በአሁን  ሰዓት የዳቦ ዱቄት ዋጋ 27 በመቶ  ጨምሯል፡፡

እናም በዚህ ሰበብ አንዳንድ የማህበሩ አባላት በኪሲራ እየሰሩ ነው ሌሎቹ ደግሞ ቤቶቻቸውን ዘግተዋል ቁጭ ብለዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ  ከመንግስት ጋር በተደጋጋሚ  ብንነጋገርበትም ለውጥ ሊመጣ አልቻለም ብሏል ማህበሩ ሲል ቢቢሲ አፍሪቃ ዘግቧል፡፡

በ2010 በሞዛቢክ በዳቦ ዋጋ ላይ 30 በመቶ ጭማሪ መታየቱን ተከትሎ በተነሳ ሁከት የ10 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 400 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጎዳት ደርሷል፡፡

ብጥብጡን ለማስቆምም መንግስት ለተወሰነ ጊዜ የዱቄት ዋጋ ድጎማ በማድረጉ የዋጋ መረጋጋት ታይቶ ነበር፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በያይኔአበባ ሻምበል

መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *