በሊቢያ ወደብ አድርገው ወደ ጣልያንና አውሮፓ ለመግባት ሙከራ በሚያደርጉ ስደተኞች መካከል በባህር ላይ በሚያጋጥሙ አደጋዎች በርካታዎቹ ለህልፈተ ህይወት መዳረጋቸው ተደጋግሞ የሚሰማ መረጃ መሆኑ ይታወቃል፡፡
አደጋው የደረሰውም ስደተኞችን ጭና በምሽት ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ ድንገት ባጋጠማት የሞተር መቃጠል ችግር እንደሆነ መረጃው አመላክቷል፡፡
ከሞቱት መካከል ብዙዎቹ በቃጠሎው ሳይሆን ውሃ ውስጥ በመግባት እንደሆነ
ነው የተገለጸው፡፡
ስደተኞቹ የሱዳን፤ የሴኔጋል፤ የሶርያ፤ የፓኪስታን፤ የሞሮኮና የግብጽ ዜግነት ያላቸው እንደሆኑ ታውቋል፡፡
የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ባወጣ መረጃ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ 2020 ከአፍሪካ በሜድትራንያን ባህር አድርገው ወደ አውሮፓ ለመግባት ሙከራ ካደረጉ ስደተኞች መካከል ከ1 ሺህ 200 በላይ የሚሆኑት ህይወታቸውን ማጣታቸውን አመላክቷል፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው፡፡
በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም











