ሂሩት አባቷ ማን ነዉ? ፊልም በቅርስነት እንዲመዘገብ ጥሪ ቀረበ፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ እንደሆነ የሚነገረዉ ሂሩት አባቷ ማን ነዉ ፊልም ከተሰራ 56 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡
ፊልሙ በሃገሪቱ ታሪክም የመጀመሪያዉ ዘመናዊ ልብ-ወለድ ፊልም እንደሆነ ይነገራል፡፡
አሁን ታዲያ የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ይህን ፊልም በቅርስነት እንዲመዘግብ የአዲስ አበባ የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ጥሪዉን አቅርቧል፡፡

ድርጅቱ ጥሪዉን ያቀረበዉ የኢትዮጵያ ፊልም ትዝታዎችና ቅኝት በሚል በሚያዘጋጀዉ የፊልም ፌስቲቫል በማስመልከት ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ ላይ ነዉ፡፡
መበግለጫዉ ላይ የ ሂሩት አባቷ ማን ነዉ ፊልም ዲጅታላይዝ ተደርጎ ከሰሞኑ ለምርቃት እንደሚበቃም ተነግሯል፡፡

ከመጋቢት 20 እስከ 25 2013 ዓ.ም ድረስ በሚቆየዉ የፊልም ፌስቲቫል ላይ ቆየት ያሉና የተመረጡ 6 ፊልሞች በድጋሚ ለተመልካቹ እንደሚቀርቡ ተገልጿል፡፡
እነዚህም ሂሩት አባቷ ማን ነዉ? አስቴር፣ረቡኒ፣ሔርሜላ፣ቀዝቃዛ ወላፈንና የወንዶች ጉዳይ መሆናቸዉ ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ፊልም ትዝታዎች ሳምንት የአዲስ አበባ ከተማ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅትና ኩራት ፒክቸርስ ኃ/የተ/የግ ማህበር በጋራ እንዳዘጋጁት ሰምተናል፡፡

በሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *