መንግስት እስከ 6 ዓመት ላሉ ህጻናት የማቆያ ቦታዎች ሊያዘጋጅ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ፕሮጀክቱ 286 ሚሊዮን ብር በጀት እንደተመደበለት ተነግሯል፡፡

በዚህም መንግስት ከ 0 እስከ 6 ዓመት ያሉ ህፃናትን መንከባከብ የሚያስችሉ የማቆያ ቦታዎችን እንደሚያዘጋጅና እንደሚንከባከብ ነዉ ገለጸዉ፡፡

የቀዳማይ ልጆች እንክብካቤ ፕሮግራም የሚል ስያሜ የተሰጠዉ ፕሮጀክቱ ትግበራዉ “መልካም ስብዕናና ብሩህ አዕምሮ ያላቸው ዜጎች ማፍሪያና ከድህነት ነፃ የሆነች ሀገር ግንባታ መሰረት ነው” በሚል የዚህ ፕሮጀክት ማስጀመርያ በነገዉ እለት ይፋ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ህጻናት ማቆያዎቹ የሚዘጋጁባቸው ተብለው በዕቅድ ደረጃ የተቀመጡት የመንግስት መስርያ ቤቶች፣ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ፣ የደሃው ማህበረሰብ ክፍል የሚገኝባቸው አካባቢዎች እንደሚሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ኋላፊ አቶ ዣንጥራር ዓባይ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቀዳማይ ልጅነት አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ታቦር ገብረ መድን እንዳሉት ደግሞ ለዚህ ስራ ከሚያስፈልገዉ በጀት 126 ሚሊዮን ብሩን መንግስት መሸፈኑን ገልጸዉ፣ ቀሪውን 160 ሚሊዮን ብር ደግሞ ሁለት ዓለምአቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች መሸፈናቸውን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ማቆያና እንክብካቤ መስጫ ቦታዎቹ በቅድምያ በአዲስ አበባ በዘጠኙ ክፍለ ከተሞች ላይ እንደሚጀመር የገለፁ ሲሆን ለአብነት ያህል በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ላይ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.