ቢላል ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር የአክሲዮን ሽያጭ መጀመሩን አስታወቀ።

ላለፉት ሶስት አመታት በምስረታ ላይ የነበረው ቢላል ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር የአክሲዮን ሽያጭ ለመጀመር የሚያስችል ፍቃድ ከብሔራዊ ባንክ ማግኘቱን አስታውቋል።

አክሲዮን ማህበሩ፣ ከወለድ ነፃ የፋይናንስ ተቋም እንደሆነና የአክሲዮን ሽያጭ መጀመሩም ነው የገለጸው ።

የቢላል ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር የመነሻ ካፒታል መቶ ሚሊዮን ብር እንደሆነም ተነስቷል።

የአንድ የአክሲዮን ዋጋ 1ሺህ ብር እንደሆነና ዝቅተኛው የአክሲዮን ድርሻ 5 ሲሆን ከፍተኛው የአክሲዮን ድርሻ ደግሞ 2ሺህ አክሲዮን ወይንም ሁለት ሚሊዮን ብር ነው ተብሏል።

የቢላል ማይክሮ ፋይናንስ የአክሲዮን ማህበር ድርሻ እንዲኖረው የሚፈልግ ማንኛውም ዜጋ 3ሺህ 300 ብር ከፍሎ መግዛት እንደሚችል ተገልጿል ።

አክሲዮን ማህበሩ፣ ድህነትን ለመቀነስ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችኝ በተለይም ሴቶችን እንደሚደግፍም ሰምተናል።

ይሁን እንጅ ፣ በአልኮል መጠጦች፣ በአደንዛዥ እፆች፣ በቁማር ላይ እንዲሁም የሼሪያን ህግ በሚጥሱ ዘርፎች ላይ እንዳማይሰራ አስታውቋል።

አክሲዮን ማህበሩ በዋናነት በገጠር የአገሪቱ አካባቢዎች በስፋት ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ተብሏል ።

የአክሲዮን ሽያጩን በቀጣዮቹ 6 ወራት ውስጥ አጠናቆ ወደ ስራ እደሚገባ ሰምተናል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *