የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እስከሚቀጥለው አመት ድረስ በአፍጋኒስታን የሚገኙት ወታደሮች ይኖራሉ ብለው እንደማያስቡ ተናግረው ፣ ይሆን እንጂ መቼ ወታደሮቹ እንደሚወጡ ትክክለኛ የጊዜ ሰሌዳ አላቀረቡም ፡፡
ባይደን ከታሊባን ቡድን ጋር በተደረገው ስምምነት መሠረት ወታደሮቿን መቼ እንደምታስወጣ ለማወቅ ሁሉም ዓይኖች በዋሺንግተን ላይ እንደነበሩ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የካቲት 2020 ባደረገው ድርድር መሰረት አሜሪካ በአፍጋኒስታን የቀሯትን 2 ሺህ 500 ወታደሮችን በሙሉ ለማስወጣት ቃል መግባቱን ዘገባው አስታውሷል ፡፡
በምላሹም ታሊባን የሚያደረሰውን ድንገተኛ ጥቃት ለመተው ቃል ገብቷል፡፡
በትላንትናው እለት ፕሬዝደንት ባይደን በኋይት ሀውስ የመጀመሪያውን ጋዜጣዊ መግለጫ ለጋዜጠኞች በሰጡበት ወቅት ነው “የግንቦት 1ን የጊዜ ገደብ ማሟላት ግን ከባድ ሊሆን ይችላል ” ያሉት ፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ.ም











