ታንዛኒያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ማጉፉሊን ለመቅበር ተዘጋጅታለች፡፡

የታንዛኒያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ዛሬ በሰሜን ምዕራብ ታንዛኒያ ውስጥ በሚገኘው የትውልድ ከተማቸው ቻቶ ስርአተ ቀብራቸው ይፈጸማል፡፡

በዋና ከተማዋ ዶዶማ ሰኞ ይፋዊ ብሔራዊ የቀብር ስነ ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በመላ አገሪቱ ውስጥ ሽኝት ተፈጽሞለታል፡፡

የ61 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፋሊ በልብ ህመም ምክንያት መሞታቸው መነገሩ ይታወሳል ብሏል ቢቢሲ አፍሪቃ፡፡

እርሳቸውን የተኩት ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሙሉሁ ሀሰን ሀገሪቱን የሚመሩ ይሆናል፡፡

ፕሬዝደንቷ ከተለያዩ አካባቢዎች የሀዘን መግለጫ ለላኩልን እና ላጽናኑን ሁሉ ምስጋና ይድረስልን በማለት የምስጋና ማስታወሻ በትዊተር ገጻቸው ላይ ፅፈዋል ፡፡

ከቀናት በፊት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ሞት አፌዘዋል የተባሉ አራት ሰዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏል እንደ ዘገባው፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *