ኤርትራ ወታደሮቿን ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት መስማማቷ ተገለጸ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በትናትናው ዕለት ወደ አስመራ ማቅናታቸው ይታወሳል።

ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት የሄዱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኤርትራ ወታደሮቿን ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት ተስማምታለች ሲሉ በፌስቡክ ገጻቸው አሳውቀዋል።

ኤርትራ ወታደሮቿን ስታስወጣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንደሚሰማራ ገልጸዋል።

ኤርትራና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ያጠናክራሉ ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ በኢኮኖሚ ጉዳዮችም በጋራ ለመስራት ፍላጎት አለን ብለዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ጥሩና እምነት ያለው ጉርብትናችንንም እናጠናክራለን ሲሉም አስፍረዋል።

በተለይ የህዝቦች ለህዝቦች መተማመንን ወደ ነበረበት ለመመለስ እንሰራለን ሲሉም በጽሁፋቸው አሳውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጽሁፋቸው ህወሀት ጎንደርና ባህርዳር ሮኬት ማስወንጨፏን አስታውሰው በተመሳሳይም ወደ አስመራ ህወሀት ያስወነጨፋቸው ሮኬቶች የኤርትራን መንግስት ማስቆጣቱን አንስተዋል።

ለዛም ነው የኤርትራ መንግስት ድንበር አልፎ ሊገባ የቻለውና ጥቃቱ ቀጣይነት እንዳይኖረው የተከላከለው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.