ኒው ሊፍ ፈርቲሊቲ ሴንተር በቴክኖሎጂ የታገዘ የመካንነት ሕክምና መስጠት ጀመረ፡፡

ማእከሉ በግል ሆስፒታል ደረጃ በቴክኖሎጂ የታገዘ የመካንነት ህክምና መስጠት መጀመሩን አስታዉቋል፡፡

ይህ የሕክምና ዘዴ ከሴቷ እንቁላል ከወንዱ ደግሞ የዘረ ፈሳሽ በመውሰድ በቤተ ሙከራ እንዲገናኙ ተደርጎ ፅንስ ከተፈጠረ በኋላ ጽንሱ ተመልሶ ማህፀን ውስጥ ሲገባ በቴክኖሎጂ የታገዘ የመካንነት ሕክምና [IVF] ይባላል።

ይህ ሕክምና እንደየ ሰዉ ቢለያይም ከ40 እስከ 50 በመቶ ሊሳካ የሚችል መሆኑን ነው የዘርፉ ባባለሙያዎች የሚናገሩት፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ይህንን በቴክኖሎጂ የታገዘ ሕክምና ሲሰጥ በአገር ውስጥ የመጀመሪያው የመንግሥት ተቋም ሲሆን ኒው ላይፍ በግል ደረጃ የመጀመርያ ያደርገዋል፡፡

ልጅ ያለመውለድ ችግር ምክንያቱ በወንዱ መሃንነት፣ በሴቷ መሃንነት ወይም በሁለቱም በኩል ባለ የመሃንነት ችግር ሊከሰት የሚችል እንደሆነም ነው የሚገለጸው፡፡

የ IVF ወይንም በቴክኖሎጂ የታገዘ የመካንነት ሕክምና ለሃገራችን ገና አዲስ በመሆኑ የዕውቀት ሽግግር ላይ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ነው የተባለው።

ኒው ሊፍ ፈርቲሊቲ ሴንተር ከዉጭ ሀገራት ከፍተኛ እውቀት እና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በማስመጣት ይህንን አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ መስጠት መጀመራቸውን ነው ያስታወቁት፡፡

ኒው ሊፍ ለዚሁ አገልግሎት ከውጪ ያስገባው ላቦራቶሪም ሆነ ቴክኖሎጂ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሁን የተደረሰበት የቴክኖሎጂ ደረጃ ለሃገራችንም ፈር ቀዳጅና ለጎረቤት ሃገራት ጭምር ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ኒው ሊፍ ፈርቲሊቲ ሴንተር ይህንን አገልግሎት በሀገር ውስጥ ለመስጠት 49 ሚሊየን ብር ወጪ ማድረጉንም አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ የውጭ ምንዛሬን ከማዳን ባለፈ በአጎራባች ሃገራት ያሉና የIVFን አገልግሎት ለሚፈልጉ ሰዎች አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ የውጭ ምንዛሬ ገቢንም በዛው መጠን ለሃገር ለማስገኝት ጥሩ እድል ነው ተብሏል፡፡

ኒው ሊፍ ፈርቲሊቲ ሴንተር ሳርቤት በሚገኝው ማእከሉ ይህንን አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡

በሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *