የጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰብ ፍትህ ተነፍገናል እያሉ ነዉ፡፡

ቤተሰቦቹ የጆርጅ ፍሎይድ ገዳይ ዴሪክ ቻውቪን ባስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርብ ቤተሰቦቹ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ውስጥ ጆርጅ ፍሎይድን በመግደል የተከሰሰው ዴሪክ ቻውቪን የፍርድ ሂደት በዚህ ሳምንት ይጀመራል ተብሏል፡፡

ዴሪክ ቻውቪን በሚኒያፖሊስ ከተማ ውስጥ ጥቁር በሆነው ፍሎይድ አንገት ላይ ተንበርክከው ከዘጠኝ ደቂቃዎች በላይ መቆየታቸው እና ለዚህም ጆርጅ ፍሎይድ መተንፈስ በመቸገሩ ለህልፈት መዳረጉ የሚታወስ ነው፡፡

ከዛም በተጨማሪ ይህ ክስተት በአሜሪካ እና በመላው ዓለም ከፍተኛ የጭካኔ ጥግ በሚል ተቃውሞ ማስነሳቱ የሚታወስ ነው፡፡

የ 45 ዓመቱ ቻውቪን ለፍርድ ከቀረቡ አራት ፖሊሶች አንዱ ነበር፡፡
በተቀሩት አራት ፖሊሶች ላይ ደግሞ እስከ 40 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት የሚያስከትለውን የሁለተኛ ደረጃን ግድያ ጨምሮ እጅግ ከባድ ክሶች ቀርበውባቸዋል፡፡

ከስራው የተባረረው ቻውቪን ጥፋተኛ አይደለሁም ሲል በጊዜው መናገሩ ይታወሳል፡፡
የጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰቦች እና ወዳጆች የፍርድ ሂደቱን ከመጀመራቸው በፊት በሚኒያፖሊስ አካባቢ የጸሎት ሥነ-ስርዓት ያካሄዱ ሲሆን አሁንም ፍትህን እንሻለን ብለዋል፡፡
ምንጭ፡ቢቢሲ

በረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *