አሜሪካን ጨምሮ 14 አገራት የኮቪድ 19 የምርመራ ውጤት አሳስቦናል ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የዚህን ቫይረስ ወረርሽኝ አመጣጥን ለማጥናት ወደ ዩሃን ያደረገውን የጉዞ የምርመራ ውጤት ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የምርመራ ሪፖርት እንደሚለው የኮሮና ቫይረስ ያመለጠው ከቻይና ላብራቶሪ ሳይሆን ከ እንስሳት ነው የሚል ነው፡፡

ይህንንም ተከትሎ አሜሪካን ጨምሮ 14 የአለም አገራት በአለም የጤና ድርጅች የምርመራ ግኝት ላይ ጥያቄ አለን፤ ጉዳዩም አሳስቦናል ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

አገራቱ እንደሚሉት አንድም የምርመራ ውጤቱ ዘግይቷል በሌላ በኩል ደግሞ የአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ግልፅኝነት የጎደለው ነው ሲሉም በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የተቃውሞ መግለጫውን ያወጡት አገራትም፣ አሜሪካ ፣ብሪታንያ ፣ጃፖን፣ እስራኤል ፣ደቡብ ኮሪያ ፣ካናዳ፣ አውስትራሊያ ፣ዴንማርክ፣ቼክ ሪፐብሊክ፣ ኢስቶኒያ፣ላቲቪያ ፤ ኖርዌይ ናቸው።

አገራቱ እንደሚሉት የቫይረሱን መነሻ ምክንያት ማወቅ የአለም አገራት ቫይረሱን ለመከላከል እና ወደፊትም ለሚመጡ ወረርሽኞች እራሳቸውንም እንዲያዘጋጁ ስለሚረዳ፣ ሪፖርቱ ጊዜውን ጠብቆና በግልፅ መረጃው ይፋ መደረግ ነበረበት ሲሉም ቅሬታቸውን ገልፀዋል።

በቻይናዋ ዉሃን ግዛት የተነሳው የኮሮና ቫይረስ፣ ከእንስሳ እንደመጣ የተነገረ ቢሆንም በሽታው እንደተከሰተ የአለም የጤና ድርጅት ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ስፍራው እንዳይገባ ቻይና መከልከሏ ይታወሳል ።

በኋላ ላይ በአለም የጤና ድርጅት የሚመራው አለም አቀፍ መርማሪ ቡድን ወደ አገሪቱ እንዲገባ ፈቅዳለች።

ይሁን እንጂ ከቫይረሱ መነሻ ጋር ተያይዞ አሁንም ድረስ ግልፅ የሆነ ነገር አልተቀመጠም እያሉ በርካታ አገራት ቅሬታቸውን እያሰሙ ይገኛሉ፡፡

በአባቱ መረቀ
መጋቢት 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *