የኒጀር ዋና ከተማ ውጥረት ነግሶባታል

ዛሬ ማለዳ በኒያሜ በፕሬዝዳንቱ ቤተመንግስት አቅራቢያ ከባድ የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተሰምቷል፡፡

የፕሬዝዳንቱ መኖሪያ እና ቢሮ የሚገኘው በቤተመንግስቱ ውስጥ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የከባድ መሳሪያ ተኩስ ልውውጡ አስራ አምስት ደቂቃ መፍጀቱን እና በኋላ ላይ በነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ድምጽ መተካቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

ሁኔታው ግራ አጋቢ ሆኖ ቀጥሏል ከተማዋም በተጠንቀቅ ላይ ትገኛለች ብሏል የቢቢሲ ዘገባ፡፡

የተኩስ ልውውጡ የተደረገው አዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ባዙም ሲመት ሊፈጸም ከ48 ሰዓት ያነሰ እየቀረው ነው፡፡

የኒጀር መንግስት እስካሁን በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ አልሰጠም፡፡

በየካቲት በተከናወነው ምርጫ ባዙም ማሸነፋቸውን ተከትሎ ታጣቂዎች የሚፈጽሙት ጥቃት እና ፖለቲካዊ ውጥረቱ ጨምሯል፡፡

በምርጫው የተሸነፉት የቀድሞ ፕሬዝዳንታቸው እና ተፎካካሪያቸው ማሃማኔ ኡስማን የምርጫውን ውጤት አጣጥለዋል ፍርድቤት ውጤቱን ቢያጸድቀውም እርሳቸው ግን እስካሁን አልተቀበሉትም፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.