የፖለቲካ ፓርቲዎች ለኦቲዝም ተጠቂ የማህበረሰብ ክፍሎች ትኩረት እየሰጡ አይደለም ተባለ፡፡

የኒያ ፋውንዴሽን መስራች የሆኑት ወ/ሮ ዘሚ የኑስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ከምርጫዉ ጋር በተያያዘ ለኦቲዝም ተጠቂዎች ትኩረት እየተሰጠ አይደለም፤ ይህን ጉዳይ ትኩረት የሰጠ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲም እየተመለከትን አይደለም ብለዋል፡፡

የኒያ ፋውንዴሽን መስራች የሆኑት ወ/ሮ ዘሚ የኑስ፣ ለኦቲዝም ተጠቂዋች የሚሆን ሰፊ የልህቀት ማዕከል ሊገነባ ስለመሆኑም በዛረዉ መግለጫቸዉ አነስተዋል፡፡

ለኦቲዝም ተጠቂዋች የሚሆነው የልህቀት ማዕከሉ የሚገነባበትን 5 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት በአዲስ አበባ ሰሚት አካባቢ መረከባቸውንና ወደ ስራ መግባታቸው ተጠቁሟል።

የሚገነባዉ ማዕከልም 250 ሚሊዮን ብር ወጭ የሚጠይቅ ሲሆን 400 ልጆችን ማስተናገድ ይችላል ተብሏል፡፡

ከዛም በተጨማሪ በዚህ ዙሪያ የተሰራው ስራ ዝቅተኛ ነው የሚሉት ወ/ሮ ዘሚ በኢትዮጲያ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የኦቲዝም ተጠቂ ይኖራል ተብሎ እንደሚገመትም ገልፀዋል።

በረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *