የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለትንሳኤ በዓል 4ሺህ 5 መቶ የቁም እንስሳትን ለማስተናገድ መዘጋጀቱን አስታወቀ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ድርጅቱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ መጪዉን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ 4 ሺ 5 መቶ የቁም እንሰሳት እርድ ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት እንደተደረገ ገልጸዋል፡፡ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የህዝብ ግንኙነት አገልግሎት አስተባባሪ አቶ አትክልቲ ገብር ሚካኤል ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ እንዳሉት በድርጅቱ መሸጫ ሱቆች ለህብረሰተቡ የስጋ አቅርቦትንም ለማድረስ በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡ ድርጅቱ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ታሳቢ […]

ልጁን በመስሪያ ቢሮው ስም የሰየመው ኢንዶኔዢያዊ አነጋጋሪ ሆኗል

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ሳሜት ዋህዩዲ ይባላል ስራውንና ስራ ቦታውን በጣም ከመውደዱ የተነሳ የስራ ክፍሉን ስም ወስዶ የልጁ መጠርያ አድርጎታል፡፡ በአሁን ሰአት የዚህ የ 5 ወር ህፃን ልጅ ስምና አባቱ የሚሰራበት የስራ ክፍል ስም ተመሳሳይ የሆነ ሲሆን ፤ስታትስቲካዊ መረጃዎች ተግባቦት ቢሮ፤ ተብለው ይጠራሉ፡፡ ገና ከማግባቱ በፊት ነው ሳሜት ልጅ ስወልድ ልጄን በስራ ክፍሌ ስም ነው የምጠራው ሲል ለራሱን ቃል […]

ኦፌኮ መንግስትና ገዥው ፓርቲ ሁሉንም አቀፍ ያልሆነ ምርጫ ከማካሄድ መጣደፉን አቁመው የዕርቅና ብሔራዊ መግባባት መድረክ እንዲያመቻቹ ጥሪ አቀረበ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ)ፖርቲ ከብሔራዊ መግባባት መሸሽ ያገራችንን ችግሮች እያባባሰና እያወሳሰበ ነው በሚል ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥቷ፡፡ ኦፌኮ እንዳለው የአገሪቱ ውስብስብ ችግሮች በብሔራዊ መግባባት ይፈቱ ዘንድ ያደረጋቸው እጅግ ብዛት ያላቸው ጥሪዎች እየተደብሰብሰ በመታለፉቸው፤ አገራችን ሊትወጣ ከማትችልበት ሁለንትናዊ መመሰቃቀል ውስጥ ገብታለች፡፡ በበኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሕዝብን ያፈናቀለ፣ ሕይወትን ያጠፋና ንብረትን ያወደመ ግጭት ተፈጥሯል፡፡ በኦሮምያ ክልል በወለጋና ጉጂ […]

ኬንያ ወደ ሕንድ የምታደርገዉን የመንገደኞች በረራ ላልተወሰነ ጊዜ አቋረጠች፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ኬንያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተዛመተ ወደአለባት ወደ ሕንድ የምታደርገዉን የመንገደኞች በረራ ላልተወሰነ ጊዜ ማቋጧን አሳወቃለች፡፡ ውሳኔው የጭነት በረራዎችን አይመለከትም ተብሏል እንደ ዴይሊ ኔሽን ዘገባ፡፡ እስካሁን እንደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እንግሊዝ እና ካናዳ ያሉ ሀገራት ወደ ሕንድ የሚደርጉትን በረራ አቋርጠዋል፡፡ ኬንያ በሚቀጥሉት 72 ሰዓታት ውስጥ ከሕንድ ወደ ኬንያ የሚመጡ መንገደኞችን በለይቶ ማቆያ ቦታ እንዲገቡ […]

ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ የቤት ስጦታ ተበረከተላቸው።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በካራማራ ጦርነት የዚያድባሬን ታንኮች በእጅ ቦንብ እንዳጋዩ የሚነገርላቸው ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤት እንደሰጣቸው ተሰምቷል። በዛሬው ዕለትም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኝ የቀበሌ ቤት እንደተሰጣቸው ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ ተናግረዋል። አሊ በርኪ ጐታ ኦሮሞ›› [አሊ በርኪ የኦሮሞ ጀግና] የተሰኘ የሻለቃ ባሻ አሊ በርኬን ህይወት የሚያስቃኝ መጽሐፍ ተጽፎላቸዋል። መፅሃፉ በ1969 እና 1970 ዓ.ም. […]

ራማፎሳ ኤኤንሲ (ANC) ሙስናን ለማስቆም አለመቻሉን አምነዋል

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ አገዛዝ ወቅት ገዥው ፓርቲ ሙስናን ለመከላከል አለመቻሉን አምነዋል፡፡ ዙማ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት በሙስና የተጠረጠሩ ክሶችን ለመመርመርና ፍትህ ለማሰጠት በቂ ስራ አልሰራም ብለዋል፡፡ ኤ.ኤን.ሲ ተጠያቂነትን ለማስፈፀም የደቡብ አፍሪቃ ህዝብ የሚጠብቀውን ያህል እንዳልሰራ በመግለጽ ሙስና የህግ የበላይነት እንዳይረጋገጥ አድርጓል ብለዋል፡፡ “ስልጣንን እና የመንግስትን ሀብቶችን […]

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ37.4 ሚሊየን ብር በላይ በሽያጭ ከተወገዱ ንብረቶች ገቢ መገኘቱን የፌደራል ንብረት ግዢ እና ማስወገድ አገልግሎት ኤጀንሲ ለኢቲዮ ኤፍ ኤም አስታወቀ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከ40 መ/ቤቶች 94 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በመሸጥ፤ 30 ሚሊዮን 204 ሺ ብር በላይ ማስወጉን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም የ25 መስሪያ ቤቶችን 360 ሎት ያገለገሉ ንብረቶችና የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ አልሙኒየምና ስቲል ፣ቁርጥራጭ ብረታብረቶችን በመሸጥ 7 ሚሊዮን 252 ሺ ብር በላይ የተገኘ ሲሆን በአጠቃላይ በዘጠኝ ወራት ጊዜ ውስጥ በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና […]

በምስረታ ላይ የሚገኘው ሂጅራ ባንክ ዋና መስሪያ ቤቱን አስመረቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት በምስረታ ሂደት ላይ የሚገኘው ሂጅራ ባንክ፣ ዋና መስሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ ደንበል ሲቲ ሴንተር ፈት ለፊት በገዛው ህንፃ ላይ አድርጓል። በምስረታ ላይ ሆኖ የራሱን ህንፃ መግዛት የቻለ የመጀመሪያው ባንክ ነውም ተብሏል። የባንኩ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት አቶ ዳዊት ቀኖ እንዳሉት፣ ባንኩን ለመመስረት አስፈላጊ የሆኑ የቅድሚያ ስራዎች አብዛኞቹ መጠናቀቃቸውን ገልፀዋል። በዚህም ከብሄራዊ […]

ቱርክ እንቅስቃሴን ሙሉ በሙሉ ለመገደብ መዘጋጀቷን አስታወቀች፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

በሃገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አስደንጋጭ ደረጃ ላይ ደርሷል ያለዉ የቱርክ መንግስት፣ ስርጭቱን ለመግታት ለጊዜዉ እንቅስቃሴን መገደብ የተሻለዉ አማራጭ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ብሏል፡፡ ይህን ተከትሎ በኢስታንቡል የሚገኙ የግብይት ማዕከላት በሸማቾች ተጨናንቀዋል፡፡ ቀደም ሲል በአዉሮፓ ሃገራት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በእጅጉ በተስፋፋበት ወቅት፣ ቱርክ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ዉጤታማ ስራ ሰርታለች በሚል በዓለም ጤና ድርጅት ስትወደስ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በአሁኑ ወቅት […]

በበዓሉ ወቅት የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ችግር እንዳያጋጥም እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ከባዕሉ ዋዜማ ምሽት 4 ሰዓት ጀምሮ እስከ በዓሉ ምሽት 4 ሰዓት ድረስ ከሲሚንቶ ፋብሪካዎች በስተቀር የኤሌክትሪክ ሃይልን በብዛት የሚጠቀሙ ድርጅቶች ከዋናው የኃይል ቋት (ግሪድ) እንዳይጠቀሙ አሳስቧል፡፡ ተቋሙ የላከልን ሙሉ መግለጫ የሚከተለዉ ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2013 ዓ.ም የትንሳዔ በዓል ወቅት ሊኖር የሚችለውን የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ችግር ለመፍታት የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ተቋሙ […]