ሀይሌ ጋርመንት አትክልት ተራ በተፈጠረ ፀብ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉ ተነገረ፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኘዉ ሀይሌ ጋርመንት አትክልት ተራ በሁለት ግለሰቦች መካካል በተፈጠረ ፀብ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

ዛሬ ጠዋት በሁለት የጉልበት ሰራተኞች መካከል የተፈጠረ አለመግባባት ወደ ጸብ አምርቶ የአንደኛዉ ህይወት ማለፉን የገለጸዉ ፖሊስ ኮሚሽኑ ገዳዩ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ጨምሮ ገልጿል፡፡

ከገዳዩ በተጨማሪም ግርግር በማስነሳትና በማባባስ ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ዉለዋል የተባለ ሲሆን

አሁን ላይ አካባቢዉ ተረጋግቶ መደበኛ ስራ መጀመሩን ፖሊስ ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *