ሱዳን 335 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ለአሜሪካ ከፈለች።

ሱዳን የአልቃኢዳ አባላት ናቸው በተባሉ አሸባሪዎች በአሜሪካ ዜጎችና ተቋማት ላይ ለደረሰው ጥቃት 335 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ለአሜሪካ መክፈሏ ታዉቋል።

የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን እንደተናገሩት የሱዳን የሽግግር መንግሥት የተጠየቀውን 335 ሚሊዮን ዶላር በሙሉ ከፍሏል።

ይህ የካሳ ክፍያ በፈረንጆቹ 1998 ናይሮቢና ዳሬ ሰላም የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎችን ባወደመው የቦምብ ፍንዳታ፣ በ 2000 በየመን የባሕር ጠረፍ አጠገብ የአሜሪካ የጦር መርከብን በከፊል ባጋየዉ የቦምብ ጥቃት ለተገደሉ ሰዎች ቤተሰቦች፣ቁስለኞችና በ2008 ካርቱም ውስጥ ለተገደለ አንድ አሜሪካዊ ቤተሰብ እንደሚከፈል ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

በኤምባሲዎቹ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ከ220 በላይ ሰዎች ሲገደሉ 4 ሺህ የሚሆኑት ቆስለዋል።

አሜሪካ በወቅቱ ለተፈጸመባት ጥቃት የአጸፋ ምላሽ የሰጠች ሲሆን፣ አል ሺፋ የተባለውን የሱዳንን የመድሐኒት ፋብሪካ በሚሳዬል አውዳማዉ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.