በብራዚል በመጋቢት ወር ብቻ ከ 60 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መሞታቸው ተነገረ፡፡

ከኮቪድ-19 ጋር በተገናኘ ከ 66 ሺህ 570 በላይ ሰዎች በብራዚል በመጋቢት ወር ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡

ይህ ቁጥር በየካቲት ወር ከነበረዉ ጋር ሲነጻጸር ከሁለት እጥፍ በላይ እንደጨመረ ያሳያል ነው የተባለው፡፡

ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ በወረሽኙ ላይ ያሳዩት ቸልተኝነት ከፍተኛ ትችት አስነስቶባቸዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተገናኘም አንድ ከፍተኛ ባለስልጣ ስልጣናቸውን በፍቃዳቸው መልቀቃቸውን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል፡፡

በሀገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ መጨመሩን ተከትሎ የህክምና ተቋማት አቅማቸው እየተፈተነ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

በሃገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ በኃላ የጤና ሚኒስትሮች ለአምስት ጊዜ ተቀያይረዋል፡፡

በትናንትናዉ እለት ብቻ በብራዚል 3 ሺህ 800 ሰዎች በዚሁ ቫይረስ ህወታቸውን ሲያጡ ከ 90ሺህ በላይ ደግሞ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡

ብራዚል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያደረሰባቸዉ ከሚገኙ ሀገራት ከቀዳሚዎቹ መካከል ተጠቃሽ ናት፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *