በታሪክ የመጀመሪያዋ ሄሊኮፕተር ከምርድ ውጩ ወዳሉ ፕላኔቶች ልትላክ ነው፡፡

የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከምድራችን ወደ ቀይዋ ፕላኔት ማርስ ሄሊኮፕተር ለመላክ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ሄሊኮፕተሯ በዚሁ ወር እንደምትላክም ናሳ ጨምሮ ገልጿል፡፡

ሄሊኮፕተሯ እንደታሰበው የማርስ ገጽ ላይ የምትደርስ ከሆነ እ.ኤ.አ በ1903 በምድራችን የ2ቱን አውሮፕላን አብራሪ ወንድማማቾች ታሪክ ከ117 አመታት በኃላ የናሳ ተመራማሪዎች ይደግሙታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የዛሬ 117 አመታት ወደኋላ በሰሜን ካሮላይና የሚኖሩ ኦልቪር ራይትና ዊልበር ራይት የተባሉ 2 ወንድማማቾች ለመጀመሪያ ጊዜ አውሮፕላን በሰማይ ላይ የተሳካ የማብረር ሙከራ በማድረግ ታሪክ ስማቸዉን አስፍሮ ይገኛል፡፡

ከአንድ ክፍለ ዘመን ቆይታ በኋላ ደግሞ ይሄው ታሪክ በማርስ ላይ አውን ሊሆን መቃረቡን ነው ናሳ ያስታወቀው፡፡

ሄሌኮፕተሯ በማርስ ላይ በሚኖራት የአጭር ጊዜ ቆይታ በዋናንት ለቀጣይ ምርምሮች የሚዉሉ ምስሎችን ፎቶ አንስታ እንደምትመለስ ተነግሯል፡፡

ቢቢሲ

በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.