በአዲስ አበባ ከተማ በየአመቱ በአማካይ ከ 3 በላይ ሰዎች የሚሞቱባቸው ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ የሆኑ መንገዶች አሁን ከአደጋ ነጻ ናቸው ተባለ፡፡

ይህንን ያለው የከተማዋ የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የመንገድ ደህንነትና ቁጥጥርን አስመልክቶ ባቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ ነው፡፡

በከተማዋ በየዓመቱ ከ40 ኪሎሜትር በላይ የእግረኞች መንገድ እየተሰራ እንደሚገኝም ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡

በተለይ ከትራፊክ አደጋዎች የመንገደኞችን ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል፣ የተረፈ ምርቶች መጣያ የነበሩ ቦታዎችን ሳይቀር የመንገድ ግንባታ ስራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ የነበራቸው የኤጀንሲው ዳይሬክተር ኢ/ር ጂሪኛ ሄርጳ እንዳሉት፤ በአዲስ አበባ ከተማ በትራፊክ አደጋ ህይታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር በያመቱ በ7 ከመቶ የነበረውን አድገት ሙሉ በሙሉ ማስቆም እንደተቻለ አስታውቀዋል፡፡

እድገቱን ከማስቆም ባላፈ ወደ 5 ከመቶ መቀነስም ተችሏል ነዉ ያሉት፡፡

በትራፊክ አደጋዎች የሞትና የጉዳት እንዲሁም የንብረት ውድመት ከሚደርስባቸው ሰዎች ውስጥ 80 በመቶዎቹ እግረኞች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ሃላፊው ለአደጋዎች መቀነስ በአብዛኛው እግረኛን ያማከሉ ስራዎች በመከናወናቸው ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በየዓመቶ ከ 3 ሺህ በላይ የመንገድ ላይ የዜብራ ምልክቶች እየተሰሩ እንደሚገኙና 100 ሺህ የሚሆኑ የትራፊክ ህጎችን ተላልፈው በተገኙ አሽከርካሪዎች ላይም እርምጃ መወሰዱንም ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም በትራፊክ አማካኝነት የሚደርሱ አደጋዎችን ለመከላከል የትራፊክ ተቋማት ጥረት ብቻ በቂ ባለመሆኑ፣ እግረኞችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እንቅስቃሴያቸዉ ሃላፊነት የተሞላበት መሆን እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.