ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ምዕራብ ሪጅን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ የኢንተርኔት አገልግሎት አስጀምሯል።

በዛሬዉ እለት ይፋ የተደረገዉ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ የኢንተርኔት አገልግሎት
የጀመረባቸው ከተሞችም ባሕር ዳርን ጨምሮ ፍኖተሰላም፣ ዳንግላ፣ እንጅባራ፣ ቡሬ፣ ደብረማርቆስ እና ቻግኒ መሆናቸዉ ተገልጿል፡፡

የጀመረው የ4 ጂ የኢንተርኔት አገልግሎት በቀጣናው የነበረውን የኢንተርኔት አገልግሎት ፍጥነት በ14 እጥፍ ያሻሽለዋል ነው የተባለው።

የተጀመረዉ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በሚገባ ለማስተዋወቅ፣ የንግድ ሥርዓቱን ለማቀላጠፍ እንዲሁም ከትምህርት፣ጤናና ኢንቨስትመንት ጋር የተያያዙ ስራዎችን በሚገባ ለማከናወን ያስችላል ነዉ የተባለዉ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንዳሉት፣ በሦስት ዓመት የዕቅድ ትግበራ ውስጥ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ የ4ጂ አገልግሎት መስጠት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በኢትዮጵያ 52 ነጥብ 7 ሚሊዮን ደንበኞች እንዳሉትም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *