ከሚቀጥለዉ ሰኞ ጀምሮ እድሜያቸዉ ከ 65 ዓመት በላይ ለሆናቸዉ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባት እንደሚሰጥ የጤና ሚንስቴር አስታወቀ፡፡

የጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በጋራ በመሆን በኮሮና ቫይረስ ስርጭትና የጥንቃቄ እርምጃዎችን በተመለከተ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸዉ፡፡

የጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንዳሉት እድሜያቸዉ ከ 65 ዓመት በላይ ለሆናቸዉ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባት ከሰኞ ጀምሮ ይሰጣል፡፡

በተጨማሪም እድሜያቸዉ 55 እና ከዚያ በላይ ሆኖ የጎንዮሽ የጤና ችግር ያለባቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎችም ክትባቱ እንደሚሰጣቸዉ ሚንስትሯ ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ ተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ወደ ሃገር ዉስጥ እንደሚገባም ሚንስትሯ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መዘናጋት እንደሚታይ የገለጹት ሚንስትሯ፣ ይህ ቸልተኝነት ዋጋ እያስከፈለን ነዉና የጥንቃቄ እርምጃዎች ተጠናክረዉ ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *