ከተሞች ላይ በስፋት ስሚስተዋለዉ ስለ አዲሱ የወባ ትንኝ ምን ያህል ያዉቃሉ?

በአለም አቀፍ ደረጃ ከዚህ ቀደም የነበረዉ የወባ ስርጭት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሚስተዋለዉ በቆላማ አካባቢዎች የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን በከተማዎች እንደሚስተዋል ታዉቋል፡፡

ለዚህ ደግሞ እንደምክንያት የሚነሳዉ የወባ በሽታን የሚያመጡ የትንኝ ዝርያዎች በመገኘታቸዉ ነዉ፡፡

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በአርማዎር ሀንሰን ምርምር ኢንቲትዩት ዉስጥ የዘርፉ ተመራማሪ ዶክተር ፍፁም ግርማ በኢትዮጵያም አዲሱ የወባ ትንኝ በከተሞች በከተሞች በስፋት እየተስተዋለ ነዉ ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የነበረዉ የወባ ትንኝ የሚራባዉ በቆላማ አካባቢዎች ቢሆንም፣ አዲሱ ትንኝ ግን በከተሞች ላይ በስፋት ይስተዋላል ያሉት ተመራማሪዉ፤ ከዚህ በተጨማሪም ይሄዉ አዲሱ ትንኝ ወባን የማስተላለፍ አቅሙ ከፍተኛ እንደሆነም አንስተዋል፡፡

አዲሱ የወባ ትንኝ በከተሞች አካባቢ በስፋት እየተራበ ከመገኘቱም ባለፈ መድሃኒቶችን የመላመድ አስቸጋሪ ባህሪን የተላበሰ በመሆኑ ለህክምና አሰጣጡ ከፍተኛ ችግር ሆኗል ነዉ የሚሉት ተመራማሪዉ፡፡

አዲሱ ወባ ትንኝ በቤት ዉስጥ በሚገኙ በማንኛዉም የዉሃ ማጠራቀሚያና መያዣ ዉስጥም ጭምር ስለሚራባ ፤በከተማም ሆነ በገጠር የሚኖሩ ዜጎች የዉሃ ማጣራቀሚያዎችን ንጽህና መጠበቅ፣ አጎበር እና የወባ መከላከያ ርጭት እንዲያደርጉም ዶክተር ፍፁም አሳስበዋል፡፡

በየዘመናቱ የሰዉ ልጅ በተለያዩ የህመም አይነቶች ይሰቃያል፤ በዚህም ምክንያት በርካቶች ህይታቸዉን ያጣሉ፤ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጫናንም ለማስተናገድ ይገደዳሉ፡፡

በተፈጥሮና በቴክኖሊጂ ዉጣ ዉረድ ዉስጥም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በርካታ የህመም አይነቶች ባህሪያቸዉን እየለዋወጡ የሰዉን ልጅ ህልዉና እየተፈታተኑ ይገኛሉ፡፡

በዓለማችን ረጅም እድሜ እንዳስቆጠሩ ከሚነገርላቸዉ የህመም አይነቶች መካከል የወባ በሽታ ቀዳሚ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

በተለይም አፍሪካን በመሳሰሉ አህጉራት ዉስጥ የወባ ስርጭት ከፍተኛ እንደሆነና ይህ ደግሞ ከዜጎች የአኗኗር ዘይቤና ከተፈጥሮ ጋር የሚያያዝ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

አሁን ላይ ይህ አዲሱ የወባ ትንኝ ከጂቡቲ ወደ አዲስ አበባ ባለዉ መስመር ላይ በሚገኙ ከተሞች ላይ በስፋት ቢስተዋልም አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎችም የአሀገሪቱ ከተሞች ስለሚራባ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊደርግ ይገባል ተብሏል፡፡

በአባቱ መረቀ
መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *