የተባበሩት አረብ ኤምሬትሶች ለትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ የሚውል የምግብ እና የመድሀኒት ድጋፍ ማድረጓን አስታዉቃለች፡፡
ሀገሪቷ 46 ሺህ ኪሎግራም የሚመዝን የምግብ እና የመድሀኒት ድጋፍ በዛሬው እለት ወደ ኢትዮጵያ እንደላከች ነው ያስታወቀችው፡፡
በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አምባሳደር ሞሀመድ ሳሊም አል ረሺድ እንደተናገሩት፣ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ያላት መሆኑን ገልጸዉ ድጋፉም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል፡፡
አምባሳደሩ በትግራይ ክልል በነበረው የህግ ማስከበር ወቅት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉትና የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ ህይወታቸው አደጋ ላይ ለሆኑ ዜጎች አስፈላጊውን ድጋፍ ሀገራቸው እያደረገች እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡
ሀገሪቷ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ማቋቋምያ የሚሆን ከምግብ እና ከመድሀኒት በተጨማሪም 5 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ከዓለም የምግብ ድርጅት ጋር በመተባበር ድጋፍ እንዳደረገችም አስታዉቃለች፡፡
ኤምሬትስ ኒውስ ኤጀንሲ
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም











