የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ1 ሚሊዮን በላይ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶችን ከቻይና ወደ ዚምባብዌ ማጓጓዙን አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ ዛሬ ከቤጂንግ ወደ ዚምባብዌ ሃራሪ 1 ሚሊዮን 56 ሺህ ክትባቶችን በአንድ በረራ ብቻ ማድረሱን ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሃላፊው ተወልደ ገ/ማርያም እንዳሉት አየር መንገዱ በአፍሪካ ባለው ተደራሽነት ቀዳሚ መሆኑን ገልጸው፤ ከቻይና ክትባቶችን ለዚምባብዌ ተደራሽ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

አየር መንገዳችን በዚሁ አጣብቂኝ ጊዜ ላይ ለአፍሪካውያን ሀገራት ክትባቶችን ተደራሽ በማድረግ ለአፍሪካውያን መንግስታት የቁርጥ ቀን ደራሽ መሆኑን አሳይቷል ነው ያሉት፡፡

በሌላ መልኩ ደግሞ ከአፍሪካውያን ሀገራት ጋር ያለንን መልካም ግንኙነት የበለጠ ያሻሽላል ብለዋል፡፡

አየር መንገዱ ከዚህ ቀደም ከቻይና የተገኙ 300 ሺህ የሚሆኑ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶችን ወደ ኢትዮጵያ ማጓጓዙ የሚታወስ ነዉ፡፡

በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *